ዛሬ በኢትዮጵያ “FAO” አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በአርብቶ-አደሩ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የሚመክር መድረክ ላይ በዩጋንዳ ካምፓላ በመገኘት በድንበር አካባቢ የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ፣ደቡብ ሱዳን፣ ኬኒያ እና ከዩጋንዳ የመንግስት አመራሮች እንዲሁም ከ IGAD እና ከ“FAO” ተወካዮች ባለድርሻ አካላት ጋር መክረናል።
በዚህም በመሠረት የሰላምና ደህንነት ሥራዎች፣ የእንስሳት ሀብት ልማት እና ጠንካራ የማህበረሰብ ትስስር በማጠናከር ዙሪያ እንዲሁም በዳሰነች ወረዳ በኦሞ ወንዝና ቱርካና ሀይቅ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ስራ ለመስራት ከ “FAO” ጋር ተግባብተናል።







