እንደ ደቡብ አትዮጵያ ክልል በኩታ ገጠም እረሻ የመኸር አዝመራ ወቅት በሰፋፊ እርሻ ላይ በወላይታ፤ በጋሞ፤ በጎፋ፤ በአሪ፤ በቡርጂ እንድሁም በደቡብ ኦሞ እና በለሎችም ዞኖች በስፋት ተሰርቷል፡፡
ዛሬ በታየው የወላይታ ዞን በሩዝ ለመጀመሪያ ጊዜ እና በስንዴ በስፋት የተገኘው ስኬት በሁሉም አከባቢዎች ልስፋፋ የሚገባ ስሆን ለቀጣይ ትምህርት የተወሰደበት እና እንደ ክልል በላቀ ብቃትና እውቀት የተፈጸመ መሆኑንም ጭምር ተገንዝበናል፡፡
ስለዚህ ከተጋገዝን፤ ከተባበርን፤ አንድ ላይ ሆነን የግብርናን እና የገጠር ትራንስፎርሜሽን እናረጋግጣለን፡፡







